Meet the Minister Meet the Minister

 

 

 

News and Updates

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴርና አዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ከኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቨሎፕምንትጋ በመተባበር እነዲሁም ከሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ለሚገኙ ህፃናትና ወላጆች ልዩ ድጋፍ አደረጉ ፡፡ (ሴ.ህ.ጉ.ሚ/ር፣ ጳጉሜ 03/2010 ዓ.ም)

”በፍቅር ተደምረን መጪውን ዘመን ለህፃናት ብሩህ እናድርግ!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ቀጨኔ ህፃናት ማሳደጊያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ህፃናት እና ወላጆችን ለመደገፍ በተዘጋጀዉ ልዩ ፕሮግራም ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ያለም ፀጋይ እንደ ገለፁት “ህፃናት ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በተለየ መልኩ ለችግር ተጋለጭና ተጎጂ እነደመሆናቸዉ መጠን እነሱን ከችገር ለመታደግ እነዲሁም በመልካም አስተዳደግና ስብዕና ታንፀዉ መብታቸዉና ደህንነታቸዉ ተጥብቆ እንዲያድጉ ለማድረግ የሁላችንም አስተዋዕፆ ወሳኝ ነዉ፡፡” በማለት አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የስነልቦና ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደረገ::

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ሴቶች ለተለያዩ ጉዳቶች የተጋለጡ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበርና ባለሙያዎችን ወደ ቦታው በመላክ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶች የስነልቦናና ማበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ከፌዴራልና ከክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ሲያካሄድ የነበረው የ2010 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ፡፡ (ሴ.ህ.ጉ.ሚ/ር፣ ነሐሴ 29/2010)

በመድረኩ የሴክተሩ የ2010 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ቅንጅታዊ አሰራርን፣ አደረጃጀቶችን ማጠናከር፣ ድጋፍና ክትትልን፣ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ፣ በኣስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ህፃናትን እንዲሁም ለሴክተሩ የሚመደበውን በጀት በተመለከተ የቡድን ውይይት ተካሄዷል፣ የነበሩ ጠንካራ ጎኖች፣ ክፍተቶችና የመፍትሔ ሃሳቦችም ተነስተዋል፡፡

Legal Framework Legal Framework

Related Links Related Links